በዚህ ገጽ ላይ የሚገኝ መረጃ በከባድ ወንጀል ጥፋተኛ ለተባሉ ሰዎች ነው፡፡
ምናልባት በከባድ ወንጀል ጥፋተኛ ከተባሉ፤ የመምረጥ መብትዎ ወደነበረበት ሊመለስ ይችላል ይሆናል፡፡ ይህም በስቴትዎ ወይም በግዛትዎ ሕግጋት እና በቅጣት ውሳኔዎ ዝርዝር ላይ የተመሠረተ ይሆናል፡፡ የቅጣት ውሳኔዎን ስለማጠናቀቅዎ እና የመለቀቂያ ሁኔታዎችዎን ስለማሟላትዎ ለማረጋገጥ ጠበቃዎን ወይም የፍርድ ቤት ወኪል ያነጋግሩ፡፡ እንዲሁም ቀደም ሲል በእስር ላይ ከነበሩ ሰዎች ጋር የሚሰራ የመብት ተከራካሪ ቡድን ጋር መነጋገር ይችላሉ፡፡ ብዙውን ጊዜ እገዛ የሚያደርጉ ጠበቆች የአሏቸው፡፡
ከወንጀል ጥፋተኝነት በኋላ የDepartment of Justice ከወንጀለኛ መቅጫ ፍርድ በኋላ ለስቴት ድምጽ አሰጣጥ ህጎች መመሪያ (በእንግሊዘኛ) ስለምርጫ መብትዎ እንዲረዱ ሊያግዝዎ ይችላል፡፡ መመሪያው እንደየ ስቴቱ ስለወንጀል ድርጊቶች እና ሌሎች ጉዳዮች ለምሳሌ በምርጫ መብትዎ ላይ ተጽእኖ ሊኖረው ስለሚችል ስለ ሙከራ ጊዜ እና አመክሮ ደረጃ በደረጃ መረጃ ይሰጥዎታል፡፡ እንዲሁም የDepartment of Justice መመሪያ ከከባድ ወንጀል ውጭ ሪከርድ ስላለባቸው ለምሳሌ ስለቀላል ጥፋት ወይም በቁጥጥር ስር የመዋል ሪከርድ ስላለባቸው ሰዎች መረጃ ያካተተ ነው፡፡
ለመምረጥ ብቁ ከመሆንዎ በፊት መመዝገብ በወንጀል መከሰስን ሊያስከትል ይችላል፡፡
አጠቃላይ መምሪያ በስቴት እና በግዛት
እያንዳንዱ ስቴት እና ግዛት በከባድ ወንጀል ጥፋተኛ ከመባል በኋላ ስለመምረጥ የተለያዩ ሕግጋት አሉት፡፡ በዚህ ስፍራ በእስር ቤት ከቆዩ በኋላ ስለመምረጥ አጠቃላይ መመሪያ ያገኛሉ፡፡ በጥፋተኝነትዎ፣ በከባድ ወንጀል ድርጊትዎ ወይም በሌሎች እርስዎን በሚመለከቱ ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ተመስርቶ መወሰድ ያለባቸው ተጨማሪ እርምጃዎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡
በእነዚህ ስቴቶች እና ግዛቶች የመምረጥ መብትዎ በወንጀል ጥፋተኝነትዎ ምክንያት ተጽዕኖ ስር አይወድቅም፦
- Maine
- Vermont
- District of Columbia
- Puerto Rico
እንዲያውም በፍርድ ቤት የተጣለብዎትን የእስር ቅጣት በመፈጸም ላይ ሳሉ እንኳን ሊመርጡ ይችላሉ፡፡ ከእነዚህ ስቴቶች ወይም ግዛቶች መካከል በአንዱ የሚኖሩ ከሆነ እንዴት መመዝገብ እንደሚችሉ ይወቁ፡፡
በእነዚህ ስቴቶች ወይም ግዛቶች ከእስር ቤት ከተለቀቁ በኋላ ወዲያውኑ ለመምረጥ ብቁ ይሆናሉ፡-
- California
- Colorado
- Connecticut
- Guam
- Hawaii
- Illinois
- Indiana
- Maryland
- Massachusetts
- Michigan
- Minnesota
- Montana
- Nevada
- New Hampshire
- New Jersey
- New York
- New Mexico
- North Dakota
- Ohio
- Oregon
- Pennsylvania
- Rhode Island
- Utah
- Washington
በሙከራ ጊዜ ወይም በአመክሮ ወይም የማንኛውም ገንዘብ ባለዕዳ ከሆኑ ማለትም የቅጣት ክፍያ፣ ወጪ ወይም ካሣ መክፈል ቢኖርብዎትም እንኳ የመምረጥ መብትዎን መልሰው ያገኛሉ፡፡
በእነዚህ ስቴቶች ወይም ግዛቶች ውስጥ የሙከራ ወይም የአመክሮ ግዜዎን ካጠናቀቁ በኋላ ለመምረጥ ብቁ ይሆናሉ፦
- Alaska
- American Samoa
- Idaho
- Kansas
- Louisiana
- Missouri
- North Carolina
- Northern Mariana Islands
- Oklahoma
- South Carolina
- South Dakota
- Texas
- U.S. Virgin Islands
- West Virginia
- Wisconsin
ከእስር ከተለቀቁ እና የአመክሮ ወይም የሙከራ ጊዜዎን ካጠናቀቁ በኋላ የመምረጥ መብትዎን መልሰው ያገኛሉ፡፡ በLouisiana ስቴት ውስጥ በሙከራ ጊዜ ላይ ሳሉ ወይም ምናልባት ከአምስት ዓመታት በላይ በአመክሮ ላይ ከነበሩ ድምጽ ለመስጠት ብቁ ይሆናሉ፡፡
ከዚህ በሚከተሉት ስቴቶች ውስጥ የእስር ቅጣትዎን ሙሉ በሙሉ ካጠናቀቁ በኋላ ለመምረጥ ብቁ ሊሆኑ ወይም ላይሆኑ ይችሉ ይሆናል፡-
- Alabama
- Arizona
- Arkansas
- Delaware
- Florida
- Georgia
- Iowa
- Kentucky
- Mississippi
- Nebraska
- Tennessee
- Virginia
- Wyoming
ከእስር ከተለቀቁ በኋላ እና የእስር ቅጣትዎን ሙሉ በሙሉ ካጠናቀቁ በኋላ የመምረጥ መብትዎን መልሰው ሊያገኙ ወይም ላያገኙ ይችሉ ይሆናል፡፡ ይህም ማለት አመክሮ፣ የሙከራ ጊዜ እና/ወይም ያለብዎትን ማንኛውንም እዳ ለምሳሌ ቅጣት፣ ክፍያ፣ ወጪዎች ወይም ካሣ መክፍልዎ ጋር ከእስር ለመውጣት ማሟላት ያሉብዎትን ሁኔታዎች በሙሉ ማሟላት አለብዎ። ምናልባት ማንኛውም ዕዳ እንዳለብዎ እርግጠኛ ካልሆኑ፤ ጠበቃዎን፣ ቅጣት በተጣለብዎ ካውንቲ ውስጥ ያለውን የህዝብ ተከላካይ ጠበቆች ቢሮን ወይም የካውንቲውን ፍርድ ቤት ይጠይቁ፡፡
በስቴትዎ ወይም ጥፋተኛ በተባሉበት ጉዳይ ዝርዝር ላይ ተመስርቶ፦
- የእስር ቅጣትዎን ካጠናቀቁ በኋላ ለመምረጥ ብቁ ሊሆኑ ይችሉ ይሆናል
- የመምረጥ መብትዎ እንዲመለስልዎ ማመልከት ሊኖርብዎ ይችላል
- በድጋሚ ለመምረጥ በፍጹም ላይፈቀድልዎ ይችላል
የስቴት እና የግዛት ሕግጋት ሊቀየሩ ይችላሉ
የመምረጥ መብቶች ላይ ያሉ ለውጦችን (በእንግሊዘኛ) ያረጋግጡ፡፡ በጣም በቅርቡ የወጣ መረጃ ለማግኘት የስቴትዎን ወይም የአካባቢውን የምርጫ መስሪያ ቤት ሊያነጋግሩ ይችላሉ፡፡ ለመጨረሻ ጊዜ እንዲዘምን የተደረገው በMarch 22, 2024 ነበር፡፡
ለመምረጥ እንዴት መመዝገብ አለብዎ
አንድ ግዜ ለመምረጥ ብቁ መሆንዎን ካረጋገጡ በኋላ መመዝገብ ይችላሉ፡፡ ምንም እንኳ ቀደም ብለው ተመዝግበው የሆኑ ቢሆንም ሊሆን በሚችል መልኩ የፖስታ አድራሻዎን ጨምሮ ምዝገባዎን ማዘመን አለብዎ፡፡ ለመመዝገብ እና ለመምረጥ ስላሉዎት አማራጮች በይበልጥ ይወቁ፡፡
አንድ ግዜ ለመምረጥ ብቁ መሆንዎን ካረጋገጡ በኋላ መመዝገብ ይችላሉ፡፡ ምንም እንኳ ቀደም ብለው ተመዝግበው የሆኑ ቢሆንም ሊሆን በሚችል መልኩ የፖስታ አድራሻዎን ጨምሮ ምዝገባዎን ማዘመን አለብዎ፡፡ ለመመዝገብ እና ለመምረጥ ስላሉዎት አማራጮች በይበልጥ ይወቁ፡፡