እንደ አዲስ የዩኤስ ዜጋ ሆኖ ስለመምረጥ

ዜግነት የመምረጥ መብት ይሰጥዎታል፡፡ 

Statue of liberty

አዲስ የዩኤስ ዜጋ እንደመሆንዎ መጠን በዩኤስ ምርጫ የመሳተፍ እድል አለዎት፡፡ መምረጥ መብትዎ ነው - እናም በማኅበረብዎ ውስጥ ለውጥ ለማምጣት ታላቅ መንገድ ነው፡፡

ለምርጫ መመዝገብ የመጀመሪያው እርምጃ ነው

መምረጥ ከመቻልዎ በፊት መምዝገብ አለብዎ፡፡ አንድ ግዜ ከተመዘገቡ በኋላ በስቴት፣ በአካባቢ እና በፌዴራል ምርጫዎች መምረጥ ይችላሉ፡፡

ዜጋ በሆኑበት ሥነ ሥርዓት ወቅት ለመምረጥ ምዝገባ አድርገው ሊሆን ይችል ይሆናል፡፡ ምናልባት እርግጠኛ ካልሆኑ፣ የምዝገባዎን ሁኔታ በኦንላይን ማረጋገጥ (በእንግሊዘኛ) ይችላሉ ወይም የአካባቢዎን የምርጫ መሥሪያ ቤት (በእንግሊዘኛ) ይጎብኙ፡፡ እርስዎ በተጨማሪ በፖስታ አማካኝነት የመራጭ ምዝገባ ደርሶዎት ሊሆን ይችል ይሆናል፡፡ ምናልባት ስምዎ ወይም አድራሻዎ ከተለወጠ፤ የመራጭ ምዝገባዎን ወቅታዊ ማድረግ አለብዎ፡፡

ምናልባት ካልተመዘገቡ፣ አይዘግዩ! የእርስዎ የዜግነት ሥነ ሥርዓት ከተካሄደ በኋላ በማንኛውም ጊዜ ለመምረጥ መመዝገብ ይችላሉ፡፡


ከመመዝገብዎ በፊት በመደበኛ ሁኔታ ዜጋ መሆንዎን እርግጠኛ ይሁኑ፡፡
ምናልባት ገና የዩኤስ ዜጋ ካልሆኑ ለመምረጥ መመዝገብ የለብዎትም፡፡ ዜጋ ያልሆኑ፣ ቋሚ ሕጋዊ ነዋሪዎችን ጨምሮ በፌዴራል፣ በስቴት እና በአብዛኛዎቹ የአካባቢ ምርጫዎች መሳተፍ አይችሉም፡፡ ዜጋ ከመሆንዎ በፊት ለመራጭነት መመዝገብ በዜግነትዎ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያስከትል ይችላል፡፡ 


ለመምረጥ እንዴት መመዝገብ እንዳለብዎ

ለመመዝገብ የምዝገባ አማራጮች አሉዎት

እያንዳንዱ ስቴት እና ግዛት ለምርጫ ለመመዝገብ የራሱን ደንብ ያወጣል፡፡ ከዚህ የሚከተሉትን ማድረግ ይችሉ ይሆናል፦ 

የመራጭ ምዝገባ የመጨረሻ ቀን ይወቁ

በብሔራዊ ምርጫ የመራጭ ምዝገባ የመጨረሻ ቀን የለም፡፡ በአንዳንድ ስቴቶች የመጨረሻው የምዝገባ ቀን ከምርጫው ቀን ከ30 ቀናት አስቀድሞ ነው፡፡ በሌሎች ስቴቶች ደግሞ በምርጫ ቀን መመዝገብ ይችላሉ፡፡ የምርጫ ቀን የሚለው አገላለጽ ማንኛውንም ምርጫ የሚመለከት ነው (የአካባቢ፣ የስቴት ወይም ብሔራዊ ምርጫ)። በስቴትዎ የመራጭ ምዝገባ የመጨረሻ ቀንን ያግኙ (በእንግሊዘኛ)፡፡ 

ስለ ዩኤስ ምርጫዎች መረጃ ያግኙ

በአካባቢ እና ብሔራዊ ደረጃ ምርጫዎ የሚፈጥረውን ተጽእኖ ይረዱ

የስቴት እና የአካባቢ ምርጫዎች ዓመቱን ሙሉ ይካሄዳሉ፡፡ በስቴት ደረጃ የገዢዎች፣ የዳኞች ወይም የስቴቱን ሕግ አውጪዎች መርጫ የሚመርጡ ሊሆን ይችል ይሆናል። በአካባቢ ደረጃ ደግሞ የከንቲባዎች እና የሌሎች የአካባቢ ባለሥልጣናት ምርጫ እያካሄዱ ሊሆን ይችል ይሆናል፡፡ አሸናፊዎቹ ዕጩዎች በማኅበረሰቡ ውስጥ በሕዝብ ትራንስፖርት እና በትምህርት ቤት በጀት ላይ ውሳኔ ያሳልፋሉ፡፡ እነዚህ ውሳኔዎች በእለት ተዕለት ሕይወትዎ ላይ ተጽዕኖ ይኖራቸዋል፡፡

በየአራት አመቱ የሚካሄድ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የዩናይትድ ስቴትስ መሪ ማን እንደሚሆን ይወስናል፡፡ ከጠቅላላ ምርጫ በፊት ለፕሬዚደንታዊው ምርጫ እጩዎችን ለመምረጥ የስቴት እና የአካባቢ የመጀመሪያ ደረጃ ምርጫዎች እና ካውከስ (በእንግሊዘኛ) ይካሄዳሉ፡፡  አጠቃላይ ምርጫ (በእንግሊዘኛ) እጩውን ይወስናል፡፡ እያንዳንዱ ስቴት የየራሱ የምርጫ ሂደት እና ደንብ አለው፡፡

የኮንግረስ ምርጫዎች በኮንግረስ ማን እንደሚወክልዎ ይወስናሉ፡፡ ኮንግረስ ሁለት ክፍሎች አሉት፡- እነሱም የዩኤስ የተወካዮች ምክር ቤት እና የዩኤስ ሴኔት ናቸው፡፡ የዩኤስ የተወካዮች ምክር ቤት አባላት በስቴት ውስጥ ያሉ ዲስትሪክቶችን ይወክላሉ፡፡ እነርሱም በየሁለት ዓመቱ ይመረጣሉ፡፡ የዩኤስ ሴኔት አባላት መላውን ስቴቶች ይወክላሉ፡፡ ለስድስት ዓመታት ያገለግላሉ፤ ነገር ግን ሁሉም በአንድ ጊዜ የሚመረጡ አይደሉም። አንዳንድ ሴኔተሮች እና ሁሉም የዩኤስ የተወካዮች ምክር ቤት አባላት በመካከለኛ ጊዜ ምርጫዎች (ወይም ዳግም ምርጫ) ላይ ይሳተፋሉ፡፡ የመካከለኛ ጊዜ ምርጫዎች በእያንዳንዱ ፕሬዚደንት የአራት ዓመታት ጊዜ መካከል ውስጥ ይካሄዳሉ፡፡

ስለድምጽ መስጫዎ ይወቁ

የሚሰጡት ድምጽ በማኅበረሰቡ ላይ ምን ዓይነት ተጽዕኖ እንደሚያሳድር በማወቅ መረጃ እንዳገኘ ሰው እንዴት መምረጥ እንዳለብዎ ይማሩ፡፡

በርካታ የምርጫ መሥሪያ ቤቶች ናሙና ድምጽ መስጫዎችን በኢንተርኔት ላይ ይለጥፋሉ፡፡ አንዳንዶች እንዲሁ በኢንተርኔት አማካኝነት ወይም በፖስታ ስለ እጩዎች እና ስለ ድምጽ እርምጃዎች መረጃ ይሰጣሉ፡፡ ለተጨማሪ መረጃ የስቴትዎን ወይም የአካባቢዎን የምርጫ ዌብሳይት ይፈትሹ፡፡

የምርጫ ሠራተኛ ለመሆን ይመዝገቡ

ክፍያ የሚከፈለው የምርጫ ሠራተኛ በመሆን ማኅበረሰብዎን ይደግፉ፡፡ የምርጫ ሠራተኛ ተግባራት በሚኖሩበት አካባቢ ላይ ተመስርቶ የተለያዩ ናቸው፡፡ በርካታ የምርጫ መሥሪያ ቤቶች ሥራዎችን የሚሰሩ የምርጫ ሠራተኞች አሏቸው፣ ከሥራዎቹም መካከል፦

  • የምርጫ ቦታ ማዘጋጀት 
  • መራጮችን መቀበል 
  • የመራጭ ምዝባን ማረጋገጥ 
  • ድምጽ መስጫን ማሰራጨት  
  • መራጮች የመምረጫ መሣሪያዎች እንዲጠቀሙ ማገዝ 
  • የምርጫ አካሄድን ማብራራት 

እንደ ምርጫ ሠራተኛ ለጊዜዎ ክፍያ ያገኛሉ፡፡ የክፍያው መጠን በቦታው ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ እንዴት የምርጫ ሠራተኛ ለመሆን እንደሚችሉ በይበልጥ ይወቁ (በእንግሊዘኛ)፡፡ 

ለአዲስ ዜጎች ስለሚሰጥ ድጋፍ

ለአዳዲስ ዜጎች ምርጫ ማድረግን ጨምሮ በልዩ ልዩ የአሜሪካ ሕይወት ገጽታዎች ላይ እገዛ የሚያደርጉ ቡድኖች አሉ፡፡ የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ፦

  • በስቴትዎ ወይም በአካባቢዎ ያለ የግዛት Office of New Americans ቢሮ ጋር ግንኙነት መፍጠር ይችላሉ፡፡
  • የአካባቢ የመሠረታዊ ትምህርት ማዕከል ፈልገው ያግኙ፡፡
  • በዩኤስ ምርጫዎች ውስጥ ልምድ ያላቸውን የሌሎች አዲስ ዜጎች ቡድኖችን ያግኙ፡፡

የቋንቋ ድጋፍ

ምናልባት እንግሊዝኛ የእርስዎ ዋነኛው ቋንቋዎ ካልሆነ እና በሌላ ቋንቋ መምረጥ ከፈለጉ፤ እገዛ ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡ በእርስዎ ቋንቋ ምን ዓይነት ድጋፍ እንደሚሰጥ ለማወቅ የአካባቢዎን የምርጫ መሥሪያ ቤት ያነጋግሩ፤ ከእነርሱም መካከል፡ 

  • በእርስዎ ቋንቋ የተዘጋጀ የምርጫ መረጃ እና ማቴሪያሎች (ለምሳሌ ድምጽ መስጫ) 
  • በእርስዎ ቋንቋ ሊያነጋግርዎ የሚችል የምርጫ ሠራተኛ (የአሜሪካን የምልክት ቋንቋ ጨምሮ)
  • በምርጫ ቦታ ለእርስዎ ሊያስተረጉም የሚችል የቤተሰብ አባል ወይም ጓደኛ

ፌዴራል ሕግጋት ለእርስዎን የምርጫ መብት ጥበቃ ያደርጋሉ

ከDepartment of Justice በየመምረጥ መብትዎ መመሪያ (በእንግሊዘኛ) አማካኝነት ስለ መምረጥ መብትዎ ጥበቃ ስለሚያደርጉ የፌዴራል ሕግጋት ይወቁ፡፡ ይህ መምሪያ በተጨማሪ በስፓንሽኛ ቋንቋ ይገኛል፡፡

የመምረጥ መብትዎን በመጠቀም ላይ ሳሉ ከዚህ ከሚከተሉት መካከል ማንኛውም ካገጠመዎ አቤቱታዎን ለDepartment of Justice ያቀርቡ (በእንግሊዘኛ)፡፦

  • ማንኛውም ሰው የመምረጥ መብትዎን ጥያቄ ውስጥ የከተተ እንደሆነ 
  • በሚኖሩት የምርጫ ቁሶች በተወሰነ ቋንቋ እንዲቀርቡ የሚጠየቅ ሆኖ ሳለ እርስዎ ግን እነዚያን ቁሶች ካላገኙ 
  • ምክንያታዊ የተደራሽነት ግልጋሎት አቅርቦቶችን ካላገኙ 

መንግሥት ድምጽዎ እንዴት በትክክል መቆጠሩን እንደሚያረጋግጥ በይበልጥ ይወቁ፡፡