የመረጡት ምርጫ ደህንነት አስተማማኝ ነው
ከመረጡ በኋላ ምን ይሆናል? የመረጡት በፖስታም ይሁን በአካል ተገኝተው፣ ተፈጻሚ የሚደረጉት ሂደቶች የመረጡት ምርጫ ደህንነት የተጠበቀ እንዲሆን ያደርጋሉ፡፡ የስቴት እና የአካባቢ መሥሪያ ቤቶች የመረጡት ምርጫ በትክክል መቆጠሩን እና ድምጽዎም ውክልና ማግኘቱን ለማረጋገጥ እርምጃዎች ይወስዳሉ፡፡
የስቴት አስተዳደሮች ምርጫዎች ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ትክክለኛ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ
አንዳንድ ፕሮቶኮሎች ከስቴት ወደ ስቴት ቢለያዩም እንኳ፤ ሁሉም ስቴቶች ከዚህ በማስከተል የተገለጹት ስርዓቶች አሏቸው፡-
- ብቁነት ያላቸው መራጮች ብቻ መምረጣቸውን ያረጋግጣሉ
- ድምጾችን በትክክል እና ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ ይቆጥራሉ
- ውጤቶች በይፋ ለህዝብ ከመገለጻቸው በፊት ውጤቶቹን ያረጋገጣሉ
- የውጭ ጣልቃገብነትን ለመከላከል ከፌዴራል አጋሮች ጋር በጋራ ይሰራሉ
- በርካታ ደረጃዎች ባለው የደህንነት አጠባበቅ አማካኝነት የምርጫዎችን ደህንነት ይጠብቃሉ
ድምጽ መስጫዎች ወረቀት የሚያዝ መዝገብ አላቸው
በመላው አገሪቱ 98% መራጮች በወረቀት ድምጽ ይሰጣሉ፡፡ የምርጫ ባለስልጣናት በተጨማሪ ከምርጫ ቀን በፊት፣ በምርጫ ወቅት እና ከምርጫ ቀን በኋላ የድምጽ መስጫዎችን ቁጥር እና የት እንዳሉ ዝርዝር መረጃ ይይዛሉ፡፡ እነዚህ መዝገቦች ድምጽ መስጫዎች አለመጭበርበራቸውን እና ተገቢ ያልሆነ አካሄድ ስለመኖሩም ለመቆጣጠር ከምርጫ በኋላ ኦዲት ለማድረግ ያገለግላሉ፡፡
ድምጽ መስጫዎች ደህንነታቸው በተጠበቀ መልኩ ይቀመጣሉ
የምርጫ ቀን ሲያበቃ፣ ድምጽ መስጫዎች፣ ሪከርዶች እና መገልገያ መሣሪያዎች ተገቢው ጥበቃ ተደርጎላቸው ወደ ምርጫ መሥሪያ ቤቶች ይጓጓዛሉ፡፡ በዚያም የምርጫ ባለስልጣናት የድምጽ መስጫዎችን ቆጥረው ያስቀምጣሉ፡፡ የፌደራል ምርጫዎች ከተካሄዱ በኋላ ድምጽ መስጫዎች በድጋሚ መቆጠር ወይም ለሌላ ድህረ ምርጫ ሂደቶች የሚፈለጉ ከሆነ በሚል ለ22 ወራት መቀመጥ አለባቸው፡፡ ድምጽ ከሰጡ በኋላ ድምጽ መስጫዎ በምን መልኩ እንደሚያዝ ይወቁ (በእንግሊዘኛ)፡፡
በፖስታ የሚላኩ ድምጽ መስጫዎች ድህንነታቸው የተጠበቀ ነው
በፖስታ ድምጽ ለመስጠት የሚፈቅዱ ስቴቶች በርካታ የደህነት መጠበቂያ እርምጃዎች አደራጅተዋል፡፡ እነዚህም እርምጃዎች ሁሉም ተመላሽ የተደረጉ ድምጽ መስጫዎች ይፋዊ መሆናቸውን እና ብቁ በሆኑ መራጮች መሞላታቸውን የሚያረጋግጡ ናቸው፡፡
የደህንነት መጠበቂያ እርምጃዎች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፡-
- ፊርማን ማመሳሰል
- የመረጃ ማጣሪያ
- ባርኮዶች
- ወተር ማርክስ
- ትክክለኛ የወረቀት ክብደቶች
የምርጫ ባለስልጣናት መራጮች በምርጫ ወቅት አንድ ድምጽ ብቻ መስጣቸውን ለማረጋገጥ ብዙ እርምጃዎችን ይወስዳሉ። ምናልባት አንድ መራጭ ከአንድ ድምጽ በላይ የሰጠ እንደሆነ (ይህም ማለት በፖስታ ድምጽ ከሰጠ እና በምርጫም ቀን በአካል ተገኝቶ ለመምረጥ ከሞከረ) የሚቆጠረው አንድ ድምጽ ብቻ ነው፡፡ በድጋሚ ድምጽ መስጠትም ሆነ ሌላን ሰው መስሎ ድምጽ የመስጠት ጉዳዮች በሚመለከታቸው ባለሥልጣናት ይመረመራሉ፡፡
ድምጽ መስጫ እና መቁጠሪያ ማሽኖች ይፈተሻሉ
የምርጫ ባለሥልጣናት የድምጽ መስጫ እና መቁጠሪያ ማሽኖችን በየወቅቱ በመመርመር በአግባቡ መስራታቸውን ያረጋግጣሉ፡፡ ከሞላ ጎደል ሁሉም ስቴቶች እና ግዛቶች የድምጽ መስጫ እና መቁጠሪያ ማሽኖችን “አመክኒዮ እና ትክክለኛነት” ይፈትሻሉ፡፡ እነዚህ ፍተሻዎች ለእያንዳንዱ እጩ የተሰጠ ድምጽ እና በድምጽ መስጫው ላይ ያለ ጉዳይ በትክክል መቆጠሩን ያረጋግጣሉ፡፡
የሚካሄዱትን ፍተሻዎች መመልከት ይችላሉ፡፡ በአካባቢዎ የአመክኒዮ እና ትክክለኛነት ፍተሻ የሚካሄደው እንዴት እንደሆነ ለማወቅ የአካባቢዎን የምርጫ ባለስልጣናት (በእንግሊዘኛ) ያነጋግሩ፡፡ አንዳንድ ስቴቶች ድምጽ መስጫዎች ቆጠራ በመካሄድ ላይ እያለ ሂደቱን በቀጥታ ስርጭት ወይም በአካል እንዲያዩ ይፈቅዳሉ፡፡
በአብዛኞቹ ስቴቶች የድምጽ መስጫ ሲስተሞች ጥቅም ላይ ከመዋላቸው በፊት Election Assistance Commission መረጋገጥ እና/ወይም Election Assistance Commission ዕውቅና በተሰጠው Voting System Test Laboratory ተፈትሸው እውቅና ማግኘት አለባቸው፡፡
የመድርጫዎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ሊያግዙ ይችላሉ
ከጭበርባሪ የስልክ ጥሪዎች ወይም አጭር የጽሑፍ መልዕክቶች ይጠንቀቁ
ምርጫዎች ሲቃረቡ ከፖለቲካ ቡድኖች የስልክ ጥሪዎች እና አጭር የጽሑፍ መልዕቶች ማግኘት የተለመደ ነው፡፡ እነዚህ ቡድኖች አንዳንድ እጩዎችን ወይም የምርጫ እርምጃዎችን እንዲደግፉ ሊያሳምኑዎ ሊሞክሩ ይችላሉ፡፡ አንዳንዶች እንዲያውም የገንዘብ አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ የእርዳታ ጥያቄ ሊያቀርቡ ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን አጭበርባሪዎች እነዚህን ተመሳሳይ ስልቶች ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡ በማስከተል ጥሪው ወይም አጭር የጽሑፍ ማጭበርበሪያ መልዕክቱ ከሮቦት መሆኑን ለማረጋገጥ የሚችሉባቸው ጥቂት መንገዶች እነዚህ ናቸው፡፦
- ደዋዩ ወይም የጽሑፍ መልዕክቱን የላከው የማኅበራዊ ዋስትና ቁጥርዎን ጨምሮ ግላዊ መረጃዎን እንዲሰጡ ይጠይቅዎታል፡፡ ቀደም ብለው በስልክ ድምጽ መስጠት እንደሚችሉ ወይም ምንም ዓይነት ስህተት ሳይኖር በመራጭ ምዝገባዎ ላይ ያለን ስህተት ማስተካከል እንደሚችሉ ይነገርዎታል፡፡ ያስታውሱ፡- በማንኛውም ስቴት በስልክ ድምጽ መስጠት፣ ምዝገባዎን ማዘመንም ሆነ ድምጽ መስጠት አይችሉም፡፡
- ደዋዩ ወይም የጽሑፍ መልዕክቱን የላከው የክሬዲት ካርድ ወይም ሌላ የገንዘብ ነክ መረጃ ጥያቄ ያቀርባል፡፡ አንዳንድ አጭበርባሪዎች ለዳሰሳ ጥናት ጥያቄ ምላሽ እንዲሰጡ የስጦታ ካርድ እንሰጣለን ሊሉ ይችላሉ፤ ሆኖም ግን ለመላኪያ ወጪ የእርስዎን የክሬዲት ካርድ መረጃ ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡ በስልክ የክሬዲት ካርድ መረጃዎችዎን ከመስጠትዎ በፊት ይጠንቀቁ፡፡
- ደዋዩ ወይም የጽሑፍ መልዕክቱን የላከው በስልክ አማካኝነት ልገሳ እንዲያደርጉ አበክሮ ይጠይቃል፤ አማራጭ የልገሳ መንገድም አይሰጥዎትም፡፡ ምናልባት ይህ የስልክ ጥሪ የማጭበርበር እንደሆነ ካሰቡ፤ በመጀመሪያ ተጨማሪ መረጃ ማግኘት የሚችሉበት ድረገጽ ያለ እንደሆነ መጠየቅን እንደ አማራጭ ይውሰዱ፡፡
የምርጫ ወንጀሎችን ሪፖርት ያደርጉ
ምናልባት ከምርጫ ጋር የተያያዙ ወንጀሎች ካጋጠሙዎ ወይም ከጠረጠሩ ሪፖርት ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡
- ጉዳዩን ለአካባቢ ለሕግ አስከባሪ ያሳውቁ፡፡
- ጉዳዩን ለስቴትዎ ወይም ለአካባቢው የምርጫ መሥሪያ ቤት ሪፖርት ያድርጉ፡፡
- ከምርጫ ጋር የተያያዙ የማጭበርበር ስልክ ጥሪዎች ወይም አጭር የጽሑፍ መልዕክቶች በሚደርሱዎ ጊዜ የአካባቢዎ Federal Bureau of Investigation ያሳውቁ (በእንግሊዘኛ)፡፡
- ማንኛውንም መራጭን የማስፈራራት ወይም የመጨቆን ሁኔታ ካለ ለDepartment of Justice የCivil Rights Division ኦንላይን (በእንግሊዘኛ) ወይም በስልክ (በእንግሊዘኛ) ያሳውቁ፡፡
ስለ ፌዴራል ምርጫ ወንጀሎች እና እንዴት ማሳወቅ እንዲችሉ በይበልጥ ይወቁ (በእንግሊዘኛ)፡፡
የሕዝብ ድምጽ መስጫ ሠራተኛ ይሁኑ
የሕዝብ ድምጽ መስጫ ሠራተኛ በመሆን ምርጫዎች በውጤታማነት እንዲካሄዱ በማገዝ ማኅበረሰብዎን ይደግፉ፡፡ የሕዝብ ድምጽ መስጫ ሠራተኞች ብዙውን ጊዜ ክፍያ እና ከአገልግሎትም በፊት ሥልጠና ይሰጣቸዋል። በማኅበረሰብዎ ውስጥ እንዴት የሕዝብ ድምጽ መስጫ ሠራተኛ መሆን እንደሚችሉ ይወቁ (በእንግሊዘኛ)፡፡
ተጨማሪ ግብአቶች
የምርጫዎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ስለሚወስዷቸው እርምጃዎች በይበልጥ ለማወቅ የአባቢዎን የምርጫ መሥሪያ ቤት ያነጋግሩ። በተጨማሪበርካታ የፌዴራል መንግሥት ኤጀንሲዎች ለድምጽዎ ጥበቃ ለማድረግ በመሥራት ላይ ናቸው፡-