የአካል ጉዳተኛ ሆኖ ምርጫ ማድረግ

ለመምረጥ ያለዎት ብቁነት በሕግ ጥበቃ ያለው ነው እናም ለእርስዎ የሚሰጡ አገልግሎቶች እነዚህ ናቸው።

A person in a wheelchair receives voting materials.

የሚመርጡት በአካልም ሆነ በፖስታ አማካኝነት ከሆነ የተደራሽነት አገልግሎቶች የማግኘት መብት አለዎት።  

ለእርስዎ ምቹ የሆነውን የምዝገባ አማራጭ ይምረጡ 

ኦንላይን ይመዝገቡ፡- አብዛኞቹ ስቴቶች በኦንላይን እንዲመርጡ እና የመራጭነት ምዝገባዎን ኦንላይን ላይ እንዲዘምን እንዲያደርጉ ይፈቅዳሉ። ምናልባት በስቴትዎ ኦንላይን ምዘገባ ያለ እንደሆነ ለማረጋገጥ ስቴትዎን ይምረጡ ስቴትዎ የምርጫው ድረገጽ ሁሉም ዓይነት የአካል ጉዳተኞች ሊጠቀሙበት የሚችሉት መሆኑን ማረጋገጥ አለበት፡፡
በፖስታ ስለመመዝገብ፦ ከNew Hampshire, North Dakota, Wisconsin እና Wyoming በስተቀር በእያንዳንዱ ስቴት ሊጠቀሙበት የሚችሉትን ብሔራዊ በደብዳቤ ምርጫ ምዝገባ ቅጽ በእንግሊዘኛ (በእንግሊዘኛ) ማውረድ፣ ማተም እና መስጠት ይችላሉ፡፡ ቅጹ በበርካታ ቋንቋዎች ይገኛል፡፡ አስፈላጊ በሚሆን ጊዜ ቅጽ ለመሙላት ጓደኛዎን ወይም የቤተሰብ አባልዎን እገዛ እንዲያደርግልዎ ይጠይቁ፡፡

በአካል ስለመመዝገብ፦ የሚከተሉትን ጨምሮ በተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች መመዝገብ ይችላሉ፦

  • የስቴት እና የአካባቢ የምርጫ መሥሪያ ቤቶች 
  • የስቴት የሞተር ተሽከርካሪ መሥሪያ ቤቶች 
  • የሕዝብ እገዛ እና የአካል ጉዳተኝነት መሥሪያ ቤቶች 
  • አንዳንድ ቤተ መጽሐፍቶች 
  • በአንዳንድ የኮሌጅ እና የዩኒቨርሲቲ ግቢዎች 

ምናልባት አስፈላጊ ከሆነ ለመመዝገብ እንዲያግዙዎት ሌላ ሰው ይዘው መምጣት ይችላሉ፡፡

በአካል ተገኝተው የሚመርጡ ወቅት ተደራሽነትን ማመቻቸት 

በአካል በሚመርጡ ጊዜ ለመምረጥ ቀላል የሚያደርግሉዎትን የተደራሽነት አገልግሎቶች የመጠየቅ መብት አለዎት።  ምን መጠየቅ እንደሚችሉ በየአካል ጉዳተኛ አሜሪካዊያኖች ህግ የምርጫ ቦታዎች ተደራሽነት ዝርዝር (በእንግሊዘኛ) ውስጥ መረጃ ያገኛሉ፡፡

በሕግ ጥበቃ ያላቸው የተደራሽነት አገልግሎቶች ምሳሌዎች ከዚህ የሚከተሉትን ያካትታሉ፦ 

  • አገልግሎት የሚሰጡ እንስሳት ድጋፍ 
  • እርስዎ እንዲመርጡ የሚያግዝዎት ሰው (አሰሪዎ ወይም የማኅበር ተወካይ ሊሆን አይችልም)
  • በምርጫ ቦታ በሁሉም ደረጃዎች ላይ የእጅ መደገፊያዎች 
  • ተደራሽ የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎች
  • የምርጫ እና የድምጽ መስጫ ቁሶች በትልልቅ ሕትመት 
  • በምርጫ ቦታዎች ስፋታቸው ቢያንስ 32 ኢንች የሆነ መገቢያዎች እና በሮች 
  • ለዊልቼር ተደራሽ የሆኑ የምርጫ ቦታዎች፤ ነገር ግን በውስጥ እና በውጪ 
  • በእያንዳንዱ ቦታ ቢያንስ አንድ ተደራሽ የምርጫ መገልገያ መሳሪያ እነዚህ መገልገያ መሳሪያዎች ማየት የተሳናቸው፣ ማየት ለሚያስቸግራቸው ወይም ሌሎች
  • የተደራሽነት እገዛ ፍላጎት ላላቸው መራጮች እገዛ ያደርጋሉ፡፡ 
  • የምርጫ ሠራተኞች የተደራሽነት የምርጫ መሣሪያዎችን እንዲጠቀሙ እገዛ ያደርጋሉ፡፡

የእርስዎ የምርጫ ቦታ (በእንግሊዘኛ) ምናልባት የሚፈልጉት የተደራሽነት አገልግሎት ያለው ስለመሆኑ ለማወቅ ከምርጫ ቀን በፊት የእርስዎን ስቴት ወይም የአካባቢ ምርጫ መሥሪያ ቤት (በእንግሊዘኛ) ማነጋገር ይችላሉ፡፡ ሲያነጋግሯቸው፣ ለእርስዎ ምርጫ ቀላል እንዲሆን ስለሚፈልጉት ነገር በግልጽ ያስረዷቸው፡፡ በተጨማሪ በእርስዎ ቋንቋ የተዘጋጀ ድምጽ መስጫ ወይም አማራጭ ቅርጸት ያለው (ለምሳሌ ህትመት ወይም በድምጽ) እንዲቀርብልዎ ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡

ምናልባት የእርስዎ የምርጫ ቦታ ለእርስዎ ተደራሽ አለመሆኑን ካወቁ፤ ስለሌሎች አማራጮች የምርጫ መሥሪያ ቤትዎን ይጠይቁ፡፡ ከዚህ የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ፡-

በፖስታ ወይም በቀሪ መራጭ ለሚካሄድ ምርጫ የሚሰጡ አገልግሎቶች 

በበርካታ ስቴቶች የምርጫ ቦታዎ ለእርስዎ ተደራሽ ካልሆነ ምናልባት በምርጫ ቀን ጉዞ የሚያደርጉ ከሆኑ ወይም ለእርስዎ በይበልጥ ትርጉም ያለው በቤት ውስጥ ሆነው መምረጥ በሚሆን ጊዜ በቀሪነት ሊመርጡ ይችላሉ፡፡ በእርስዎ ስቴት የቀሪ ምርጫ ለማካሄድ ጥያቄ ያቅርቡ (በእንግሊዘኛ) አንዳንድ ስቴቶች ምርጫ የሚያካሄዱት ሙሉ በሙሉ በፖስታ ነው፡፡ 

በስቴትዎ በፖስታ በሚመርጡበት ጊዜ ለእርስዎ ሊኖሩ ከሚችሉ አገልግሎቶች አንዳንዶቹ ከዚህ የሚከተሉት ናቸው፦

  • የምርጫ ቁሶች በአማራጭ ቅርጸት ለምሳሌ በትልልቅ ህትመት ወይም በድምጽ
  • አማራጭ የፊርማ መስፈርት፤ ለምሳሌ ፊርማዎን ታይፕ ማድረግ 
  • ተደራሽ የሆነ የሩቅ ድምጽ መስጫ ስርዓት፡፡ ይህ አማራጭ ምርጫውን በኤሌክትሮኒክ ዘዴ እንዲያደርጉ፣ እንዲያትሙ እና ከዚያ በማስከተል በኢሜል እንዲልኩ ወይም ወደ ምርጫ መሥሪያ ቤትዎ መልሰው እንዲያመጡ ያስችልዎታል፡፡

የምርጫ መስጫዎን መልሰው ለማምጣት ዕቅድ ያለዎ መሆንዎን እርግጠኛ ይሁኑ፡፡ በስቴት ሕግጋት ላይ ተመስርቶ የድምጽ መስጫዎን በፖስታ፣ በምርጫ መስጫ ሳጥን ማስገባት ወይም ሌላ ሰው እንዲያስገባልዎ ማድረግ ይችላሉ፡፡ ኤሌክትሮኒክ የምርጫ ምላሽ (በእንግሊዘኛ) በእርስዎ ስቴት ሊኖር የሚችል ሌላው አማራጭ ነው፡፡ ይህ አማራጭ ድምጽዎን በፖስታ፣ በፋክስ ወይም ኦንላይን ፖርታል ለመላክ ያስችልዎታል፡፡ 

የአካል ጉዳተኝነት ላለባቸው መራጮች ተጨማሪ ጥቆማዎች እና ግብአቶች 

በሚመርጡበት ጊዜ በአካል ጉዳተኝነት ምክንያት መድልዖ ደርሶብኛል ብለው ካመኑ ለDepartment of Justice ያጋጠመዎትን ሁኔታ ሪፖርት ያድርጉ (በእንግሊዘኛ)፡፡

የፌደራል ሕግጋት የእርስዎን የመምረጥ መብትዎን ጥበቃ ያደርጋሉ፡፡

በርካታ የፌዴራል ሕግጋት የአካል ጉዳተኝነት ላለባቸው አሜሪካዊን የመመዝገብ እና የመምረጥ መብት ጥበቃ ያደርጋሉ፡፡

ለመምረጥ መብትዎ ጥበቃ ስለሚያደርጉ የፌዴራል ሕግጋት ከDepartment of Justice የመምረጥ መብትዎ መመሪያ (PDF) (በእንግሊዘኛ) ይወቁ፡፡

ለመምረጥ ዝግጁ ነዎት?

የመራጭ ምዝገባ የመጨረሻ ቀን ይወቁ

በብሔራዊ ምርጫ የመራጭ ምዝገባ የመጨረሻ ቀን የለም፡፡ በአንዳንድ ስቴቶች የመጨረሻው የምዝገባ ቀን ከምርጫው ቀን ከ30 ቀናት አስቀድሞ ነው፡፡ በሌሎች ስቴቶች ደግሞ በምርጫ ቀን መመዝገብ ይችላሉ፡፡ የምርጫ ቀን የሚለው አገላለጽ ማንኛውንም ምርጫ የሚመለከት ነው (የአካባቢ፣ የስቴት ወይም ብሔራዊ ምርጫ)። በስቴትዎ የመራጭ ምዝገባ የመጨረሻ ቀንን ያግኙ (በእንግሊዘኛ)፡፡ 

የመራጮች መለያ መስፈርቶች

እያንዳንዱ ስቴት እና ግዛት የየራሱን የመራጭ መለያ ደንቦች ያወጣል፡፡ በአብዛኛዎቹ ስቴቶች በአካል ተገኝተው መምረጥ መታወቂያዎን ይዘው መቅረብ፤ በፖስታ አማካኝነት ሲመርጡ ደግሞ የማንነትዎን መረጃ መስጠት አለብዎ፡፡ የስቴትዎን የመራጭ መታዊቂያዎች መስፈርቶችን ያረጋግጡ (በእንግሊዘኛ)፡፡

ምንም እንኳን የማያሽከረክሩ ቢሆንም ከስቴትዎ የሞተር ተሽከርካሪ መሥሪያ ቤት መታወቂያ ማግኘት ይችላሉ፡፡ መታወቂያ ለማግኘት ክፍያ መፈጸም ይኖርብዎታል፤ ነገር ግን ከመታወቂያ ጋር ለተያያዙ ክፍያዎች ምናልባት እገዛ ሊያደርጉልዎ የሚችሉ ድርጅቶች አሉ፡፡

ድምጽ ለመስጠት የመራጭ መለያ ካርድ አያስፈልገዎትም፡፡

የቋንቋ ድጋፍ

ምናልባት እንግሊዝኛ የእርስዎ ዋነኛው ቋንቋዎ ካልሆነ እና በሌላ ቋንቋ መምረጥ ከፈለጉ፤ እገዛ ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡ በእርስዎ ቋንቋ ምን ዓይነት ድጋፍ እንደሚሰጥ ለማወቅ የአካባቢዎን የምርጫ መሥሪያ ቤት ያነጋግሩ፤ ከእነርሱም መካከል፡ 

  • በእርስዎ ቋንቋ የተዘጋጀ የምርጫ መረጃ እና ማቴሪያሎች (ለምሳሌ ድምጽ መስጫ) 
  • በእርስዎ ቋንቋ ሊያነጋግርዎ የሚችል የምርጫ ሠራተኛ (የአሜሪካን የምልክት ቋንቋ ጨምሮ)
  • በምርጫ ቦታ ለእርስዎ ሊያስተረጉም የሚችል የቤተሰብ አባል ወይም ጓደኛ

የምርጫ ሠራተኛ ለመሆን ይመዝገቡ

ክፍያ የሚከፈለው የምርጫ ሠራተኛ በመሆን ማኅበረሰብዎን ይደግፉ፡፡ የምርጫ ሠራተኛ ተግባራት በሚኖሩበት አካባቢ ላይ ተመስርቶ የተለያዩ ናቸው፡፡ በርካታ የምርጫ መሥሪያ ቤቶች ሥራዎችን የሚሰሩ የምርጫ ሠራተኞች አሏቸው፣ ከሥራዎቹም መካከል፦

  • የምርጫ ቦታ ማዘጋጀት 
  • መራጮችን መቀበል 
  • የመራጭ ምዝባን ማረጋገጥ 
  • ድምጽ መስጫን ማሰራጨት  
  • መራጮች የመምረጫ መሣሪያዎች እንዲጠቀሙ ማገዝ 
  • የምርጫ አካሄድን ማብራራት 

እንደ ምርጫ ሠራተኛ ለጊዜዎ ክፍያ ያገኛሉ፡፡ የክፍያው መጠን በቦታው ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ እንዴት የምርጫ ሠራተኛ ለመሆን እንደሚችሉ በይበልጥ ይወቁ (በእንግሊዘኛ)፡፡