የተደራሽነት መግለጫ

የተደራሽነት መግለጫውን ከvote.gov እናት ኤጀንሲ ማለትም ከGeneral Services Administration (በእንግሊዘኛ) ያንብቡ፡፡

Vote.gov ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ቁርጠኛ ነው፡፡ የአካል ጉዳተኝነት ያለባቸውን ሰዎች ጨምሮ የምርጫ ግብአቶች ለእያንዳንዱ ሰው ተደራሽ መሆናቸውን ማረጋገጥ ፖሊሲያችን ነው፡፡

Vote.gov የአካል ጉዳተኝነት ያለባቸው ሰዎች በድረ ገጽ ላይ መረጃዎች ተደራሽ እንዲሆኑላቸው ከሚጠሙባቸው መገልገያዎች ጋር በሚገባ እንዲሰራ በተወሰኑ ቴክኖሎጂዎች ይደገፋል፡፡ እነዚህ ቴክኖሎጂዎች HTML፣ WAI-ARIA፣ CSS እና JavaScriptን ይካተታሉ፡፡ እነዚህ ቴክኖሎጂዎች vote.govን በስክሪን አንባቢዎች፣ በስክሪን ማጉያዎች፣ በንግግር መለያ ሶፍትዌር እና በሌሎች አጋዥ ቴክኖሎጂዎች አማካኝነት ለመጠቀም ቀላል መሆናቸውን ለማረጋገጥ ያስችላል፡፡
 

ይዘት

የተደራሽነት መግለጫ

የvote.gov ቡድን የማየት፣ የመስማት፣ የኮምፒውተር ሃርድዌር የመጠቀም ችግር ወይም የመገንዘብ እና ትምህርት የመቅሰም ተግዳሮት ያጋጠማቸውን ሰዎች ጨምሮ ተደራሽ ድረ ገጽ ለመፍጠር ቁርጠኛ ነው፡፡ እኛ በተጨማሪ ዋነኛ ቋንቋቸው አንግሊዝኛ ያልሆነ ሰዎችን ጨምሮ በቂ አገልግሎት የማያገኙ ሰዎችን ለመድረስ እንጥራለን፡፡ ተደራሽነት ቀጣይነት ያለው ጥረት ነው እናም እኛ የድረገጹን ይዘት ለሚጽፉልን፣ ሰነዶቻችንን ለሚያዘጋጁ እና ድረገጻችንን ለሚያጎለብቱ ሠራተኞቻችን ሥልጠና በመስጠት vote.gov እንዲሻሻል ጥረት እናደርጋለን፡፡

ተደራሽነትን እንዴት እንደምንደግፍ እና እንደምናስቀጥል

ከዚህ በሚከተሉት መንገዶች vote.gov ተደራሽ መሆኑን እናረጋግጣለንን፦ 

  • ለኪቦርድ እና ለስክሪን አንባቢ ተደራሽነት ይዘትን በእጅ በመፈተሽ
  • ይዘቱን ለማደራጀት የፍቺ ክፍል ርዕሶችን በመጠቀም
  • ሁሉንም የድረገጻችን አገናኞች እና መስተጋብራዊ ክፍሎች ያገኙ ዘንድ ሰዎች ኪቦርዱን እንዲጠቀሙ በመፍቀድ 
  • በዚህም ስር “ወደ ዋናው ይዘት ይሸጋገሩ” የሚለውን ይካተታል 
  • ለስክሪን አንባቢዎች "በአዲስ መስኮት እየተከፈተ" እንደሆነ ለማሳወቅ ወደ ውጫዊ ሊንኮች ኮድ በመጨመር 
  • ለምስሎች፣ ለአዶዎች እና ለአርማዎች ዝርዝር አማራጭ ጽሑፍ በማቅረብ
  • አውድ እና የተጠቃሚ ተሞክሮ ለማቅረብ ሰዎችን በይዘት ትርጉም ውስጥ በማሳተፍ
  • ተጠቃሚዎች እንደምርጫቸው የጽሁፍን መጠን እንዲቀይሩ በመፍቀድ 

የእኛ የተደራሽነት ደረጃዎች

ድረገጻችንን የነደፍነው በክፍል 508 (በእንግሊዘኛ) የተቀመጡትን ደረጃዎች እንዲያሟላ ወይም ከዚያም የተሻለ እንዲሆን ለማድረግ ነው፤ እነዚህ መስፈርቶች የፌዴራል ሕግ ክፍል 508ን ስለማክበራችን እንደ ቴክኒክ መስፈርት የሚያገለግሉ ናቸው፡፡ እንዲሁም ከአለም አቀፍ ዌብ ኮንሰርቲየም (W3C፣ የድሩ የበላይ አካል) እና የእነሱ የዌብ ይዘት ተደራሽነት መመሪያዎች (WCAG) 2.1፣ ይህም በ W3C ድረገጽ (በእንግሊዘኛ) ላይ ሊገኝ ይችላል፡፡ እኛ የደረጃ AA መመዘኛዎችን እናሟላለን፤ ይህ ማለት ይዘታችን በአብዛኛዎቹ ሁኔታዎች ውስጥ ላሉ ለብዙ ሰዎች ተደራሽ ነው።

አማካሪ እና ፍተሻ

ተደራሽነትን ለመመዘን እና ለማሻሻል በአውቶሜትድ እና በማኑዋል ዘዴ በቀጣይነት ኦዲቶችን የሚያደርግ ገለልተኛ ባለሙያ አማካሪ አለን፡፡

የአካል ጉዳተኝነት ካለባቸው ሰዎች ጋር በመሆን መደበኛ የአጠቃቀም ፍተሻ እናካሂዳለን፤ በዚህም ግበረ መልስ አማካኝነት ማሻሻያዎችን እናደርጋለን፡፡

ሳይቱን በአዳዲስ የተደራሽነት ገጽታዎች እያዘመንን በሄድን ቁጥር ይህንን የተደራሽነት መግለጫ እናሻሽላለን፡፡ ከወደፊት ዕቅዶቻችን መካከል ሰዎች ድረገጹ እንዴት መምሰል እንዳለበት እና ለማተምም አማራጮችን በራሳቸው መንገድ እንዲወስኑ ማስቻልን ያካትታል፡፡

ተኳኋኝነት

  • Vote.gov Chromeን፣ Firefoxን፣ Edgeን እና Safariን ጨምሮ ከአብዛኞቹ ዋና የበይነመረብ አሳሾች ጋር ተኳሃኝ ነው።
  • የVote.gov ይዘት በስማርትፎን፣ በታብሌት፣ በላፕቶፕ ወይም በዴስክቶፕ ላይ ሊታይ ይችላል። 

ባካሄድናቸው ኦዲቶች ወይም ፍተሻዎች ማንኛውም ዓይነት የተደራሽነት ውስንነት አላገኘንም፡፡ ሆኖም ግን vote.gov በመንግሥት ባለቤትነት ያልተያዙ ወይም በመንግሥት የገንዘብ ድጋፍ ከማይደረግላቸው የምርጫ ግብዓቶች ጋር ይገናኛል፡፡ ይህን የምናደርገው እንዲህ ያሉት ድረ ገጾች ምናልባት በመንግሥት ይፋዊ ድረገጽ ላይ የማይገኙ መንግሥታዊ መረጃዎችን የያዙ ከሆነ ነው፡፡ እነዚህን የመንግሥት ያልሆኑ ድረገጾችን ልንቆጣጠር አንችልም፡፡ እንዲህ ባሉት ድረገጾች ላይ ያሉት መረጃዎች ትክክለኛ፣ አግባብነት ያላቸው፣ ጊዜያቸውን የጠበቁ ወይም የተሟሉ ናቸው የሚል ዋስትና ልንሰጥ አንችልም፡፡ 

የተደራሽነት እገዛ፣ ግብረ መልስ እና መደበኛ ቅሬታዎች

Section508-vote@gsa.gov ለእኛ ኢሜል በማድረግ በvote.gov አጠቃቀም ጊዜ ስላጋጠመዎ ሁኔታ ማንኛውም ግብረ መልስ ላኩልን፡፡ ቡድናችን ለጥያቄዎችዎ፣ አስተያየቶችዎ ወይም ስጋቶችዎ በሁለቱም ማለትም በእንግሊዝኛ እና በስፓኒሽኛ ቋንቋ መልስ መስጠት ይችላል።

Touchpoints ID: votegov-accessibility-survey

እኛን ለማግኘት ሲፈልጉ እባክዎን የሚከተሉትን ያካትቱ፦

  • የዌብ አድራሻ በተጨማሪ URL በመባልም ይታወቃል። ዓይነተኛ የሆነ URL http://example.gov/index.html ወይም https://www.example.gov/exampleሊሆን ይችላል፡፡
  • vote.govን ለማግኘት እየተጠቀሙበት ያለው መገልገያ መሳሪያ እና አሳሽ
  • እየተጠቀሙበት ያለው አጋዥ ቴክኖሎጂ፤ ምናልባት ካለ
  • የችግሩ ዝርዝር እና ማንኛውም ተደራሽ ስላልሆነ መረጃ

ማስታወሻ፦ ከፌዴራል በዓላት ወይም መስሪያ ቤቱ ካልተዘጋ በስተቀር ከሰኞ እስከ አርብ በምስራቃዊ ሰዓት አቆጣጠር በመደበኛ የስራ ሰዓታት Section508-vote@gsa.govን እንቆጣጠራለን፡፡

በችግሩ ላይ ተመስርቶ የvote.gov 508 ቡድን እስከመቼ እንደሚስተካከል እንዲጠብቁ ይገልጽልዎታል፡፡

ለተጨማሪ የተደራሽነት አገዛ ከዚህ በታች የሚገኘውን ቅጽ በእንግሊዝኛ ወይም በስፓኒሽኛ ይሙሉ፡፡

ማንኛውንም የvote.govን ይዘት ተደራሽነት አስመልክቶ ጥያቄዎች፣ አስተያየቶች ወይም ቅሬታዎች ካለዎ ወደ Section508-vote@gsa.gov ኢሜይል ይላኩ።

ተጨማሪ የተደራሽነት ግብአቶች አሉ

ምናልባት ከዚህ ከሚከተሉትን ለማድረግ ፍላጎት ካለዎ በGSA የተደራሽነት ድረገጽ (በእንግሊዘኛ) ላይ የሚከተሉትን በይበልጥ ይወቁ፦

ገጹ እንደገና የታየው እና እንዲዘምን የተደረገው May 2024 ነው፡፡